ቤልጅየም፡ግለሰቡ በሞት እያጣጣረ ሲስቁ የነበሩ ፖሊሶች ጉዳይ ቁጣን ቀሰቀሰ
- GH ETHIO NEWS
- Aug 20, 2020
- 1 min read
ጉዳዩ የተፈጸመው በቤልጅየም ሻርሎይ ከተማ ነው፡፡
ጆዜፍ ቻፋኖቫ የሚባል የስሎቫኪያ ዜግነት ያለው ሰው በሻርሎይ አየር መንገድ ውስጥ ችግር ፈጥረሃል በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ይውላል፡፡
ግለሰቡ በብስጭት ራሱን ከግድግዳ ጋር እያጋጨ (ደም በደም እስኪሆን ድረስ) ጥፋተኛ እንዳልሆነ በአንድ ክፍል ውስጥ ላገቱት ፖሊሶች ይናገራል፡፡
እነሱ ግን ሰውየውን ከመርዳት ይልቅ ሲስቁበት ነበር፡፡ ሊሞት እያጣጣረ ሳለም አንደኛው ፖሊስ የናዚ ሰላምታን እየሰጠ ሲስቁበት ይታያል፡፡
ይህ ጭካኔ የተሞላበት የሲሲቲቪ ቪዲዮ ሾልኮ የወጣው አሁን ቢሆንም ጉዳዩ የተፈጸመው ግን በየካቲት 2018 ዓ.ም እንደ አውሮጳዊያኑ አቆጣጠር ነው፡፡
ቪዲዮው ከተለቀቀ በኋላ ነገሩ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

ባሏን በዚህ መንገድ ያጣችው ስሎቫኪያዊት ነገሩ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ፍትሕ እንድታገኝ ጠይቃለች፡፡
ሟች ፖሊሶች በቁጥጥር ካዋሉት በኋላ በንዴት ራሱን ከግድግዳ ጋር ሲያጋጭ በርካታ ፖሊሶች ማጅራቱን ቆልፈው አንዲት መሬት ላይ ሲደፍቁት ይታያሉ፡፡
ቾቫንኮቫ በዚህ ስቃይ ውስጥ እያለ ፖሊሶቹ ሲያሾፉበት ይሰማሉ፡፡ በኋላ ላይ ሆስፒታል በወሰድም በነገታው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
ቾቫንኮቫ በዚያ ስቃይ ውስጥ ሆነው ከሚስቁበት ፖሊሶች ሌላ አንዱ ፖሊስ ሟችን ፊቱን በብርድልብስ ከሸፈነ በኋላ ደረቱ ላይ ቁጭ ብሎበት ቪዲዮ ሲቀርጽ ነበር፡፡
ሌላ የፖሊስ ባልደረባው ደግሞ የናዚ ሰላምታ ሲሰጥ ይታያል፡፡
ይህ ቪዲዮ ሟች በአንዲት ጠባብ ክፍል ከታገተ በኋላ የነበረውን የ18 ደቂቃ ሁኔታ የሚያስቃኝ ነው፡፡
የቾቫንኮቫ አሟሟት ከጆርጅ ፍሎይድ ጋር የሚያመሳስሉት አልጠፉም፡፡
‹‹እኔ ባሌ ላይ በትክክል ምን እንደተፈጠረና ለምን ፖሊሶች እንደዚያ እንደጨከኑበት ማወቅ እፈልጋለሁ ብላለች ባለቤቱ ሄንሪታ ቪዲዮን ላጋለጠው የአገሬው ጋዜጣ፡፡
ሟች ቾቫንኮቫ በቤልጅየም ውስጥ የሕንጻ ተቋራጭ ኩባንያዎች የስሎቫክ ሰራተኞቸን የሚያስቀጥር ድርጅት ነበረው፡፡ በዚህም የተነሳ ከአገሩ ወደ ቤልጅየም ብዙ ጊዜ ይመላለስ ነበር፡፡
በ2008 በሬሳው ላይ የተደረገ ምርመራ ሟች ባህሪውን ሊቀይር የሚችል የመጠጥም ሆነ ሌላ አደገኛ እጽ እንዳልወሰደ ያረጋግጣል፡፡
ሟች አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ ሁከት ፈጥረኻል በሚል ነበር በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለው፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ የሻርሎይ ፖሊስ በምስሉ ላይ የናዚ ሰላምታ ሲሰጥ የነበረውን ፖሊስ ከሥራ እንዳባረረው ገልጧል፡፡
የሻርሎይ ከተማ አቃቤ ሕግ በበኩሉ ሁሉም በሟች ላይ ሲሳለቁ የነበሩ ፖሊሶችን ቃል መቀበሉንና በኮቪድ ምክንያት ምርመራው መዘግየቱን ጠቅሶ ፍርድ ይዘግይ እንጂ ፍርድ እንደሚሰጥ ግን ተናግሯል፡፡
Comments